ምሳሌ 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያለ ነውር የሚመላለስ ተማምኖ ይሄዳል፥ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐቀኛ ሰው ያለ ሥጋት ይራመዳል፤ በጠማማ ጐዳና የሚሄድ ግን ይጋለጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁሉም ነገር ታማኝ ሰው ያለ ስጋት ይኖራል። የጠማማ ሰው እርምጃ ግን ይጋለጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል። |
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።