ምሳሌ 1:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእናንተ መጥፋት እስቃለሁ፥ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም መከራ በእናንተ ላይ በሚደርስባችሁ ጊዜ እስቅባችኋለሁ፤ ችግር በሚደርስባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እኔ በጥፋታችሁ እሥቃለሁ፤ ጥፋትም በመጣባችሁ ጊዜ ደስ ይለኛል። |
ጌታ እናንተን በማበልጸግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ ጌታ እናንተን ሲያጠፋችሁና ሲያፈራርሳችሁም ደስ ይለዋል፤ እንድትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ትነቀላላችሁ።