ዘኍል 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለቀዓት ልጆች ግን በትከሻቸው በመሸከም ቅዱስ የሆኑትን ነገረሮች ማገልገል የእነርሱ ነበርና፥ ለእነርሱ ምንም አልሰጣቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው መሸከም ስለ ነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው፥ በኰረብታ ላይ ካሚገኘው ከአቢናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ ሠረገላውን ይነዱ የነበሩትም የአቢናዳብ ልጆች ዖዛና አሒዮ ነበሩ፤
ታቦቱንም፥ ገበታውንም፥ መቅረዙንም፥ መሠዊያዎቹንም፥ ካህናቱም የሚገለገሉባቸውን የመቅደሱን ዕቃዎች፥ መጋረጃውንም፥ መገልገያውንም ሁሉ ይጠብቃሉ።