ዘኍል 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕድሜው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያለውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገባውን ሁሉ ትቈጥራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቍጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ የሚደርሰውን ወንዶች ሁሉ መዝግብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በምስክሩ ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትለያለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በመገናኛው ድንኳን ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡበትን ሁሉ ትደምራለህ። |
በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሸአልቲኤል ልጅ ዘሩባቤል፥ የዮፃዳቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ምርኮኞች ሁሉ፥ ሌዋውያንንም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የጌታን ቤት ሥራ እንዲቆጣጠሩ መረጧቸው።
ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።
የእስራኤል አምላክ ከእስራኤል ማኅበር የለያችሁ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት እንድትሠሩ፥ እንድታገለግሉአቸውም በማኅበሩ ፊት እንድትቆሙ ወደ እርሱ ለማቅረብ መፍቀዱን እንደ ቀላል ነገር ቈጠራችሁትን?
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው።
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው።
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቈጠሩአቸው፤
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራውን ለመሥራትና ዕቃውን ለመሸከም የገቡት ሁሉ፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉት፥
ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ የተነገረውን ትንቢት ሁሉ መሠረት በማድረግ፥ በእነርሱ መልካም ውጊያን እንድትዋጋ ይህችን ትእዛዝ በአደራ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤