ዘኍል 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንዲሁም በመቅደሱ ውስጥ ለአገልግሎት የሚሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ በአቆስጣ ቍርበት በመሸፈን በመሸከሚያው ሳንቃ ላይ ያስቀምጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመቅደሱ መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ ወስደው በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑአቸው፤ የለፋ ስስ ቊርበት ደርበውም በመሸከሚያው ተራዳ ላይ ያኑሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመቅደስም ውስጥ የሚያገለግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፤ በሰማያዊዉም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፤ በአቆስጣም ቍርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፤ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመቅደስም ውስጥ የሚያገልግሉበትን የማገልገያውን ዕቃ ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡት፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑት፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉት። |
ጉጠቶቹንም ድስቶቹንም ሙዳዮቹንም ጀሞዎቹንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። የውስጠኛውም ቤት የቅድስተ ቅዱሳን ደጆች የቤተ መቅደሱም ደጆች የወርቅ ነበሩ።
በእርሱም ላይ የአስቆጣውን ቁርበት መሸፈኛ ያድርጉበት፥ ከእርሱም በላይ ሁለንተናው ሰማያዊ የሆነ መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፥ መሎጊያዎቹንም ያግቡ።
በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።
ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤