Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 25:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እኔ እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ድንኳኑ ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ልክ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ዕቃዎች ሁሉ እኔ በማሳይህ ዕቅድ መሠረት ሥሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 25:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ለመስራት ጥንቃቄ አድርግ።”


ማደሪያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም።


የመገናኛው ድንኳን የማደሪያው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ። የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ፤ እንዲሁ አደረጉ።


የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ።


ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆ ልክ ጌታ እንዳዘዘው አድርገውት ነበር፤ እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።


በመቅደስም ውስጥ የሚገለገሉባቸውን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይውሰዱ፥ በሰማያዊውም መጐናጸፊያ ውስጥ ያስቀምጡአቸው፥ በአቆስጣም ቁርበት መሸፈኛ ይሸፍኑአቸው፥ በመሸከሚያውም ላይ ያድርጉአቸው።


መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ ከእግሩ እስከ አበቦቹ ድረስ ሥራው ተቀጥቅጦ የተሠራ ነበረ፤ ጌታ ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አድርጎ ሠራው።


“እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤


እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።


ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ።


ድንኳን ተዘጋጅቶ ነበር፥ በእርስዋም ውስጥ ቅድስት በምትባለው መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበር።


ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ሲሆን፥ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም የማያደርጉ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች