ገባዖናውያንም፥ “በእኛና በሳኦል ወይም በእኛና በቤቱ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፥ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፥ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
ዘኍል 35:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቁ ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ እንዲመለስ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ሰው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ስለ ገባ ስለ ማንኛውም ሰው የደም ዋጋ በመቀበል ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዶ እዚያ እንዲኖር አታድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ቢያመልጥ ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ዘንድ ገንዘብ እንዲከፍል አትፍቀዱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁ ካህን እስኪሞት ወደ ምድሩ ትመልሱት ዘንድ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ዋጋ አትቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋነኛው ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ ይመለስ ዘንድ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ። |
ገባዖናውያንም፥ “በእኛና በሳኦል ወይም በእኛና በቤቱ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፥ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፥ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።