ዘኍል 32:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጦርነት ተዘጋጅተን በጌታ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጦርነት ዝግጁ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ እዚሁ ይሆናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእርሱም መሪነት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ በዚህ በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የርስት ድርሻችንን ለራሳችን ለማስቀረት ወደ ጦርነት እንሄዳለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጦር መሣሪያችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ ከዮርዳኖስም ማዶ የወረስነው ርስት ይሆንልናል” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል አሉት። |
ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና ከተሞቹን በከተሞቹም ዙሪያ ያሉትን ግዛቶች ሰጣቸው።
በዮርዳኖስ ማዶ በምድረ በዳ፥ በዓረባ ትይዩ በሆነው ሱፍ ፊት ለፊት፥ በፋራን እና በጦፌልም፥ በላባንም በሐጼሮትም በዲዛሃብም መካከል ሳሉ፥ ሙሴ ለእስራኤል ሁሉ የነገራቸው ቃል ይህ ነው።
በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው።
የእስራኤልም ልጆች ያሸነፉአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን አገራቸውን የወረሱአቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
የጌታ ባርያ ሙሴና የእስራኤል ልጆች አሸነፉአቸው፤ የጌታም ባርያ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች ለጋድም ልጆች ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።