Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 32:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ከነ​ዓን ምድር እን​ሻ​ገ​ራ​ለን፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ የወ​ረ​ስ​ነው ርስት ይሆ​ን​ል​ናል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ለጦርነት ዝግጁ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ እዚሁ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ለጦርነት ተዘጋጅተን በጌታ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በእርሱም መሪነት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ በዚህ በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የርስት ድርሻችንን ለራሳችን ለማስቀረት ወደ ጦርነት እንሄዳለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 32:32
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው።


“ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።


ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።


“ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ እኔ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ርስት ወደ ከነ​ዓን ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እኔም የለ​ምጽ ደዌ ምል​ክት በር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቤቶች ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥


ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወዲህ ወደ ምሥ​ራቅ ርስ​ታ​ችን ደር​ሶ​ና​ልና እኛ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ​ዚያ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ርስት አን​ወ​ር​ስም።”


እነ​ዚህ ሁለቱ ነገ​ድና የአ​ንዱ ነገድ እኩ​ሌታ ርስ​ታ​ቸ​ውን በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በም​ሥ​ራቅ በኩል ወረሱ።”


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በም​ድረ በዳ፥ በም​ዕ​ራብ በኩል በኤ​ር​ትራ ባሕር አጠ​ገብ በፋ​ራ​ንና በጦ​ፌል፥ በላ​ባ​ንና በአ​ው​ሎን፥ በካ​ታ​ኪ​ሪ​ሲ​ያም መካ​ከል፥ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ የነ​ገ​ራ​ቸው ቃላት እኒህ ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የመ​ቱ​አ​ቸው፥ ከአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አር​ሞ​ን​ዔም ተራራ ድረስ በም​ሥ​ራቅ በኩል ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ በፀ​ሐይ መውጫ ያለ​ውን ሀገ​ራ​ቸ​ውን የወ​ረ​ሱ​አ​ቸው የም​ድር ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ ርስት አድ​ርጎ ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለጋ​ድም ልጆች፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች