ዘኍል 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ዔር ማደሪያ የተዘረጋው በሞዓብም ዳርቻ የሚገኘው የሸለቆች ተዳፋት መሬት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዔር የሚወስዱት በሞዓብ ድንበርም የሚገኙት የሸለቆች ተረተሮች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ዔር ከተማና እስከ ሞአብ ወሰን የሚዘልቁት ሸለቆዎች ሸንተረር” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዒር ማደሪያ የሚወርድ፥ በሞዓብ ዳርቻም የሚጠጋ የሸለቆዎች ፈሳሾችንም አቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዔር ማደሪያ የሚወርድ በሞዓብም ዳርቻ የሚጠጋ የሸለቆች ፈሳሽ። |
ጌታ አምላካችን ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ፥ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አድርግልኝ።’”
ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”