Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ አምላካችን ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ፥ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አድርግልኝ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልን ሁሉ፣ አንተም አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክንሻገር ድረስ እንደዚሁ አድርግልን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በኤዶም የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ የሞአብ ዘሮች በግዛታቸው በኩል እንድናልፍ እንደ ፈቀዱልን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረን እግዚአብሔር ወደሚያወርሰን ምድር እስክንገባ ድረስ በዚያ ለማለፍ ፍቀድልን።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:29
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤዶምያስም፦ “በምድሬ ላይ አታልፍም አለበለዚያ ግን አንተን በሰይፍ ልገጥምህ እወጣለሁ” አለው።


ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑርህ።


እንግዲህ አንተ ልበ ደንዳና ሕዝብ ነህና ጌታ አምላክህ ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳልሆነ እወቅ።


“ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ ጌታ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”


በእናንተ ቃላት ምክንያት ጌታ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።


“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።


ጌታም አለኝ፦ ‘እኔ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ፥ ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ በውጊያም አትጋፈጣቸው።’”


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።


እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’


ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር በለዓምን መስማት አልፈለገም፥ ጌታ እግዚአብሔር ወድዶሃልና እርግማኑን በረከት አደረገልህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች