ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
ዘኍል 18:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተመረጠውንም ከእርሱ ባቀረባችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤልን ልጆች የተቀደሱ ነገሮች አታረክሱም።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተመረጠውን ክፍል ካቀረባችሁ በዚህ በደለኞች አትሆኑም፤ ደግሞም የተቀደሰውን የእስራኤላውያንን መባ አታረክሱም፤ አትሞቱምም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምርጥ የሆነውን ነገር ለእግዚአብሔር ካቀረባችሁ በኋላ በምትመገቡበት ጊዜ በደል አይኖርባችሁም፤ ነገር ግን ምርጥ የሆነው ነገር ከእርሱ ላይ ሳይነሣ ከስጦታው በመመገብ የእስራኤላውያንን የተቀደሰ ስጦታ እንዳታስነውሩ ተጠንቀቁ፤ ይህን ብታደርጉ ግን ትሞታላችሁ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢአት አይሆንባችሁም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታርክሱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተመረጠውንም ከእርሱ ባነሣችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኃጢአትን አትሸከሙም፤ እንዳትሞቱም የእስራኤል ልጆች የቀደሱትን አታረክሱም። |
ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
“የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ ለአሮንና ለልጆቹ ተናገር፤ እኔ ጌታ ነኝ።
“በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታቀርባላችሁ።” እናንተም፦ “ያረከስንህ እንዴት ነው?” ትላላችሁ። “የጌታ ገበታ የተናቀ ነው” በማለታችሁ ነው።