ዘፀአት 28:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም43 አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 አሮንና ልጆቹ ዘወትር ወደ ድንኳን ሲገቡ ወይም በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ ይለብሱታል፥ በዚህ ዐይነት የውስጥ ሰውነታቸው ስለማይጋለጥ ከሞት ይድናሉ፤ ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር ሥርዓት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው እንዳይሞቱም፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል። ምዕራፉን ተመልከት |