ሌላም ጊዜ በዓልሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ገብስ የተጋገሩ ኻያ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት ለኤልሳዕ ይዞለት መጣ፤ ኤልሳዕም “ለነቢያት ጉባኤ አቅርብላቸውና ይብሉ” ብሎ አገልጋዩን አዘዘው፤
ዘኍል 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታ የሚያመጡት በምድራቸው ያለው ሁሉ የፍሬ መጀመሪያ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር የሚያመጡት የምድሪቱ በኵር ፍሬ ሁሉ የአንተ ይሆናል። ከቤተ ሰዎችህ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይህን መብላት ይችላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምድራቸው ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚያመጡት በኲራት ሁሉ የእናንተ ዕድል ፈንታ ስለሚሆን ንጹሕ የሆነ የቤተሰባችሁ አባል ሁሉ ሊመገበው ይችላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው ያለው የፍሬ መጀመሪያ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔር የሚያመጡት በምድራቸው ያለው ሁሉ የፍሬ መጀመሪያ ለአንተ ይሆናል፤ በቤትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብላው። |
ሌላም ጊዜ በዓልሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ገብስ የተጋገሩ ኻያ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት ለኤልሳዕ ይዞለት መጣ፤ ኤልሳዕም “ለነቢያት ጉባኤ አቅርብላቸውና ይብሉ” ብሎ አገልጋዩን አዘዘው፤
ይህንም ነገር እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች የእህሉንና የወይኑን ጠጅ የዘይቱንና የማሩንም፥ የእርሻውንም ፍሬ ሁሉ በብዛት ሰጡ፤ የሁሉንም አሥራት በብዛት አቀረቡ።
በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ በሁለተኛውም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።
የበኩራቱ ሁሉ መጀመሪያ፥ ስጦታ ሁሉ፥ ስጦታዎቻችሁ ሁሉ፥ ለካህናት ይሆናል፤ በቤትህም ውስጥ በረከት እንዲያድር የሊጣችሁን በኵራት ለካህን ትሰጣላችሁ።
እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ እንደ ወይን ዘለላ ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እንዳለ እንደ በለስ በኵራት በበለስ ዛፍ ላይ ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ባዓል-ፌዖር መጡ፥ ለእፍረትም ነገር ራሳቸውን ለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥
ከየማደሪያችሁ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ ከሆነ መልካም ዱቄት የተሠራ ሁለት የመወዝወዝ እንጀራ ታመጣላችሁ። ለጌታ ለበኵራት ቁርባን እንዲሆን በእርሾ ተቦክቶ ይጋገራል።
የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።
ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።