ዘኍል 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላስገባኸንም፥ እርሻና የወይንም ተክል ቦታ አላወረስከንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህም በቀር አንተ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር አላመጣኸንም፤ ወይም ዕርሻዎችንና የወይን ተክል ቦታዎች አላወረስኸንም። ታዲያ የእነዚህን ሰዎች ዐይን ታወጣለህን? በጭራሽ አንመጣም!” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ አለቃ ነህን? ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አገባኸንን? እርሻንና የወይን ቦታንስ አወረስኸንን? የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላገባኸንም፥ እርሻና ወይንም አላወረስኸንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዓይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም አሉ። |
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ።
ከግብጽም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ።’
ከግብፃውያን እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወደ መልካምና ሰፊ አገር፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ከነዓናውያን፥ ሒቲያውያን፥ ኤሞራውያን፥ ፌርዛውያን፥ ሒዊያውያን፥ የቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ነገር ግን እኔ እንዲህ አልኋችሁ፦ ‘ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እንድትወርሱአትም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ።’ እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤
አሞናዊው ናዖስ ግን፥ “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ።