ዘኍል 11:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በማግስቱም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ ዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ የሚህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት ቀንና ሌሊቱን በሙሉ፣ በማግስቱም ሙሉውን ቀን እንደዚሁ ሕዝቡ ወጥቶ ድርጭቶች ሰበሰበ፤ ከዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ ያነሰ የሰበሰበ ማንም አልነበረም፤ የሰበሰቡትንም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በዚያን ቀንና ሌሊት፥ እንዲሁም በማግስቱ ሕዝቡ ድርጭት እያሳደዱ በመያዝ ደከሙ፤ ከዐሥር ኪሎ ግራም ያነሰ የሰበሰበ አልነበረም፤ እንዲደርቁም በሰፈር ዙሪያ አሰጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ሁሉ፥ በሌሊትም ሁሉ፥ በነጋውም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ ዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ ያህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አስጥተው አደረቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በነጋውም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ አሥር የቆሮስ መስፈሪያ የሚህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። |
የኢፍና የባዶስ መስፈሪያ አንድ ይሁን፤ የባዶስ መስፈሪያ የቆሮስ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ፥ የኢፍ መስፈሪያውም የቆሮስ መስፈሪያ አንድ አሥረኛ ይሁን። መለኪያው የቆሮስ መስፈሪያ ይሁን።