ዘኍል 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳይታኘክ የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ጌታም ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት መታ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ነገር ግን ሥጋው ገና በጥርስና በጥርሳቸው መካከል ሳለ አላምጠው ሳይውጡት የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት ክፉኛ መታ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 የሚበሉት ሥጋ ገና በብዛት ሳለ፥ እግዚአብሔር በሕዝቡ እጅግ ተቈጣ፤ ብርቱ መቅሠፍትም በሕዝቡ መካከል አመጣ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት አጠፋቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ መቅሠፍት እጅግ መታ። ምዕራፉን ተመልከት |