ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።
ዘኍል 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች እንደ ሆኑ የምታውቃቸውን የእስራኤል ሽማግሌዎች የሆኑ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር በየቦታቸው ይቁሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ መካከል በመሪነትና በእልቅና ብቃት አላቸው የምትላቸውን ሰባ የእስራኤል ሽማግሌዎች አምጣልኝ፤ ካንተም ጋራ ይቆሙ ዘንድ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዲመጡ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለሕዝብ አመራር በመስጠት የታወቁ ሰባ ሽማግሌዎችን ምረጥ፤ እነርሱንም ሰብስበህ ወደ መገናኛው ድንኳን አምጣቸውና በአጠገብህ ይቁሙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች፥ ለሕዝቡ ሽማግሌዎችና ጸሐፍት ይሆኑ ዘንድ የምታውቃቸውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፤ ወደ ምስክሩም ድንኳን አምጣቸው፤ በዚያም ከአንተ ጋር አቁማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ከእስራኤል ሽማግሌዎች፥ በሕዝቡ ላይ ሽማግሌዎችና አለቆች ይሆኑ ዘንድ የምታውቃቸውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብስብልኝ፥ ወደ መገናኛውም ድንኳን አምጣቸው፥ በዚያም ከአንተ ጋር አቁማቸው። |
ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ መስራት የሚችሉ ሰዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የዐሥር አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎች ቆመው ነበር፥ የሻፋን ልጅ ያአዛንያ በመካከላቸው ቆሞ ነበር፥ እያንዳንዱም በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ መልካም መዓዛ ያለው የዕጣኑም ጢስ ወደ ላይ ይወጣ ነበር።
እኔም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን አለቆች ተቀበልኩ፥ በእናንተም ላይ የሺህ አለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የኀምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም ገዢዎችም በየነገዶቻቸው አደረግኋቸው።