እናንተ በግብጽ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገሩ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፥ እርሱንም እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
ዘኍል 10:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኛም ጋር ብትሄድ ጌታ ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኛ ጋራ ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛም እናደርግልሃለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኛ ጋር አብረህ ብትሄድ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ ለአንተም እናካፍልሃለን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኛም ጋር ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛ ለአንተ እናደርጋለን አለ። |
እናንተ በግብጽ ምድር እንግዶች ነበራችሁና ከእናንተ ጋር የሚቀመጥ እንግዳ እንደ አገሩ ተወላጅ አድርጋችሁ ተመልከቱት፥ እርሱንም እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱት፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።
የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።
በዚያን ጊዜ ቄናዊው ሔቤር፥ ዐማች የአባብ ልጆች ከሆኑት ከሌሎቹ ቄናውያን ተለይቶ በቃዴስ አጠገብ ጻዕናይም ከተባለ ቦታ ከሚገኘው ባሉጥ ዛፍ አጠገብ ድንኳኑን ተክሎ ነበር።
ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።