ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
ነህምያ 3:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ጀምረው እስከ “የበግ በር” ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች አደሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማእዘኑ በላይ ከሚገኘው ክፍል ጀምሮ እስከ በጎች በር ያለውን ደግሞ ወርቅ አንጥረኞቹና ነጋዴዎቹ መልሰው ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎችም ከቅጽሩ ማእዘን ጀምሮ እስከ በጎች ቅጽር በር ያለውን የመጨረሻውን ክፍል ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከማዕዘኑም መውጫ ጀምረው እስከ በጎች በር ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከማዕዘኑም መውጫ ጀምረው እስከ በጉ በር ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች አደሱ። |
ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
ሊቀ ካህኑ ኤልያሺብና ወንድሞቹ ካህናት ተነሥተው “የበግ በር” ሠሩ፤ ቀደሱት፥ በሩንም አቆሙ፤ እስከ “ሜአ ግንብ” እና እስከ “አሐናንኤል ግንብ” ድረስ ቀደሱት።
ከእርሱም በኋላ የወርቅ አንጥረኛው ልጅ ማልኪያ ከ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ቤት፥ የነጋዴዎቹ ቤት ጀምሮ እስከ “የመሰብሰቢያ በር” ፊት ለፊት ያለውንና እስከ ማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ድረስ አደሰ።
በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዚኤል አደሰ። በአጠገቡም የሽቶ ቀማሚዎች ልጅ ሐናንያ አደሰ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን አደሱ።