Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 3:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከእርሱም በኋላ የወርቅ አንጥረኛው ልጅ ማልኪያ ከ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ቤት፥ የነጋዴዎቹ ቤት ጀምሮ እስከ “የመሰብሰቢያ በር” ፊት ለፊት ያለውንና እስከ ማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ድረስ አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከርሱ ቀጥሎ ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ መልክያ በመቈጣጠሪያው በር ትይዩ እስከሚገኘው እስከ ቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት፣ እንዲሁም ከማእዘኑ በላይ እስከሚገኘው ክፍል ያለውን መልሶ ሠራ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ወርቅ አንጥረኛው ማልኪያ ተከታዩን መስመር ከቅጽሩ ማእዘን ሰሜናዊ ምሥራቅ ጫፍ አጠገብ እስካለው መቈጣጠሪያ ቅጽር በር በኩል የቤተ መቅደሱ ሠራተኞችና ነጋዴዎች እስከሚገለገሉበት ስፍራ ድረስ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ከእ​ር​ሱም በኋላ የሰ​ራፊ ልጅ መል​ክያ እስከ ናታ​ኒ​ምና እስከ ነጋ​ዴ​ዎቹ ቤት ድረስ በሐ​ሜ​ፍ​ቃድ በር አን​ጻር ያለ​ውን እስከ ማዕ​ዘኑ መውጫ ድረስ ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ከእርሱም በኋላ ከወርቅ አንጥረኞቹ የነበረ መልክያ እስከ ናታኒምና እስከ ነጋዴዎቹ ቤት ድረስ በሐሚ ፍቃድ በር አንጻር ያለውን እስከ ማዕዘኑ መውጫ ድረስ አደሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 3:31
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚካኤል ልጅ፥ የበዓሤያ ልጅ፥ የመልክያ ልጅ፥


ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ።


ከማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ጀምረው እስከ “የበግ በር” ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች አደሱ።


በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዚኤል አደሰ። በአጠገቡም የሽቶ ቀማሚዎች ልጅ ሐናንያ አደሰ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን አደሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች