ነህምያ 12:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 ከ “ኤፍሬም በር” በላይ፥ ከ “አሮጌው በር” በላይ፥ በ “ዓሣ በር” በ “ሐናንኤል ግንብ”፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ በጎች በር ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም በዘበኞች በር አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 ከዚያም አልፈን የኤፍሬም ቅጽር በር፥ የይሻና ቅጽር በር፥ የዓሣ ቅጽር በር ተብለው ወደተሰየሙትና የሐናንኤል ግንብ የመቶዎቹ ግንብና የበጎች ቅጽር በር ተብለው ወደሚጠሩት ስፍራዎች መጣን፤ ሰልፋችንንም ያበቃነው ለቤተ መቅደሱ ቅርብ ወደ ሆነው የዘበኞች ቅጽር በር ወደሚባለው ቦታ ስንደርስ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር፥ በአናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 በአሮጌው በርና በዓሣ በር በሐናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፥ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ። ምዕራፉን ተመልከት |