ማቴዎስ 23:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገበያ ቦታ ሰላምታና በሰዎች ደግሞ መምህር ተብለው መጠራትን ይፈልጋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታና በሰዎች አንደበት ‘መምህር’ ተብለው መጠራትን ይወድዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየአደባባዩም ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣቸውና ‘መምህር ሆይ!’ ብሎ እንዲጠራቸው ይፈልጋሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገበያም ሰላምታና ‘መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!’ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። |
በሚያስተምርበትም ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ከጸሐፍት ተጠንቀቁ፤ የተንዘረፈፈ ቀሚስ ለብሰው መዞርን ይወዳሉ፤ በየአደባባዩም የአክብሮት ሰላምታ ይሻሉ፤
ጴጥሮስም ኢየሱስን፥ “መምህር ሆይ፥ እዚህ ብንኖር ለእኛ መልካም ነው፤ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ለኤልያስ የሚሆኑ ሦስት ዳሶች እንሥራ” አለው።
ኢየሱስም መለስ ብሎ ሲከተሉትም አይቶ “ምን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ረቢ!፥ (ሲተረጎም ‘መምህር ሆይ’ ማለት ነው) የምትኖረው የት ነው?” አሉት፤
እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ “መምህር ሆይ! ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ካልሆነ በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል ማንም የለምና፤” አለው።
ወደ ዮሐንስም መጥተው “መምህር ሆይ! በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ፤” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱም “መምህር ሆይ! ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአትን የሠራው ማን ነው? እርሱ ነው ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።