Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 23:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በገበያም ሰላምታና ‘መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!’ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እንዲሁም በገበያ ስፍራ የአክብሮት ሰላምታና በሰዎች አንደበት ‘መምህር’ ተብለው መጠራትን ይወድዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በገበያ ቦታ ሰላምታና በሰዎች ደግሞ መምህር ተብለው መጠራትን ይፈልጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በየአደባባዩም ሰው ሁሉ እጅ እንዲነሣቸውና ‘መምህር ሆይ!’ ብሎ እንዲጠራቸው ይፈልጋሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በገበያም ሰላምታና፦ መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 23:7
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዘወር ብሎ ሲከ​ተ​ሉት አየና፥ “ምን ትሻ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማር​ያም!” አላት፤ እር​ስ​ዋም መለስ ብላ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለ​ችው፤ ትር​ጓ​ሜ​ዉም “መም​ህር” ማለት ነው።


በባ​ሕሩ ዳርም ባገ​ኙት ጊዜ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ወደ​ዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።


ወደ ዮሐ​ን​ስም ሄደው፥ “መም​ህር ሆይ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነ​በ​ረው፥ አን​ተም የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ለት እርሱ እነሆ፥ ያጠ​ም​ቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄ​ዳል” አሉት።


እር​ሱም በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “መም​ህር ሆይ፥ ልታ​ስ​ተ​ምር ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ መጣህ እና​ው​ቃ​ለን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ይህን ተአ​ምር ሊያ​ደ​ርግ የሚ​ችል የለ​ምና።”


ኢየሱስም መልሶ “ምን ላደርግልህ ትወዳለህ?” አለው። ዕውሩም “መምህር ሆይ! አይ ዘንድ፤” አለው።


ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን “መምህር ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ፤” አለው።


እናንተ ግን ‘መምህር’ ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።


ነገር ግን “ይህን ትውልድ በምን እመስለዋለሁ? በገበያ የሚቀመጡትን ልጆች ይመስላሉ፤ እነርሱም ባልንጀሮቻቸውን እየጠሩ


አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም መልሶ “መምህር ሆይ! እኔ እሆንን?” አለ፤ “አንተ አልህ፤” አለው።


ወዲያውም ወደ ኢየሱስ ቀረበና “መምህር ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” ብሎ ሳመው።


ጴጥሮስም ትዝ ብሎት “መምህር ሆይ! እነሆ፥ የረገምሃት በለስ ደርቃለች፤” አለው።


ሲያስተምርም እንዲህ አለ “ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን፥ በገበያም ሰላምታን፥ በምኵራብም የከበሬታን ወንበር፥ በግብዣም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ፤


መጥቶም ወዲያው ወደ እርሱ ቀረበና “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ!” ብሎ ሳመው፤


እና​ንተ ግብ​ዞች ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያን፥ ወዮ​ላ​ችሁ! በም​ኵ​ራብ ፊት ለፊት መቀ​መ​ጥን፥ በገ​በ​ያም እጅ መነ​ሣ​ትን ትወ​ዳ​ላ​ች​ሁና።


በዚ​ህም ጊዜ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ እህል ብላ” ብለው ለመ​ኑት።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደው በማን ኀጢ​ኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወ​ላ​ጆቹ?” ብለው ጠየ​ቁት።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም፥ “መም​ህር ሆይ፥ አይ​ሁድ ሊወ​ግ​ሩህ ይሹ አል​ነ​በ​ረ​ምን? ዛሬ ደግሞ አንተ ወደ​ዚያ ልት​ሄድ ትሻ​ለ​ህን?” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች