ማቴዎስ 14:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እነዚያን ወደዚህ ወደ እኔ አምጡልኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እስኪ ያለውን ወደ እኔ አምጡት” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡልኝ!” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “እነዚያን ወደዚህ አምጡልኝ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እነዚያን ወደዚህ አምጡልኝ አላቸው። |
ሕዝቡን በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።
እርሱም፥ መሬት ላይ እንዲቀመጡ ሕዝቡን አዘዘ፤ ሰባቱን እንጀራ ይዞ ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ ለሰዎቹ እንዲያድሉ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለሕዝቡ አደሉት።
ኢየሱስም “ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ፤” አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ፤ ቁጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር።