ዮሐንስ 6:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ኢየሱስም “ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ፤” አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ፤ ቁጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ኢየሱስም፣ “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉ” አለ። በዚያ ቦታ ብዙ ሣር ነበረ፤ ዐምስት ሺሕ ያህል ወንዶችም ተቀመጡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ኢየሱስም “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉአቸው” አለ። በዚያ ቦታ ብዙ ሣር ነበረ፤ ሰዎቹም ተቀመጡ፤ ቊጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያኽል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ” አለ፤ የዚያ ቦታም ሣሩ ብዙ ነበር፤ ወንዶቹም በመስኩ ላይ ተቀመጡ፤ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ ያህል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ኢየሱስም፦ ሰዎቹን እንዲቀመጡ አድርጉ አለ። በዚያም ስፍራ ብዙ ሣር ነበረበት። ወንዶችም ተቀመጡ ቍጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያህል ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |