ራሱን በሳሕን መጥቶ ለልጅቱ ተሰጣት፤ እርሷም ወደ እናትዋ ወሰደችው።
የተቈረጠውም ራስ በሳሕን ላይ ተደርጎ ለብላቴናዪቱ ተሰጣት፤ ብላቴናዪቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።
የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን አምጥተው ለልጅቱ ሰጡአት፤ እርስዋም ለእናትዋ ወስዳ ሰጠች።
ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፤ ወደ እናትዋም ወሰደችው።
ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው።
ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።
ቁጣ ጭካኔን ያስከትላል፥ ንዴትም እንደ ጎርፍ ነው፥ በቅንዓት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
ደምን ለማፍሰስ የሚሹ ሰዎች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፥ እንዲሁም የቅኑን ሰው ነፍስ ይሻሉ።
ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።
ልኮም የዮሐንስን ራስ በእስር ቤት አስቆረጠው።
ደቀ መዛሙርቱም መጥተው በድኑን ወሰደው ቀበሩት፤ መጥተውም ለኢየሱስ ነገሩት።
እርሷም በእናትዋ ተመክራ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ ሳሕን አሁን ስጠኝ” አለችው።
የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤”
ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት። ባየኋትም ጊዜ በእጅጉ ተደነቅሁ።