Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን አምጥተው ለልጅቱ ሰጡአት፤ እርስዋም ለእናትዋ ወስዳ ሰጠች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የተቈረጠውም ራስ በሳሕን ላይ ተደርጎ ለብላቴናዪቱ ተሰጣት፤ ብላቴናዪቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ራሱን በሳሕን መጥቶ ለልጅቱ ተሰጣት፤ እርሷም ወደ እናትዋ ወሰደችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፤ ወደ እናትዋም ወሰደችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 14:11
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰዎች የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው፤”


ያቺ ሴት በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየኋት፤ ባየኋትም ጊዜ እጅግ በጣም ተደነቅሁ።


ስለዚህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ ለግድያ አዘጋጃችኋለሁ፤ ገዳይም ያሳድዳችኋል፤ ደም ማፍሰስን ስላልጠላችሁ ገዳይ ያሳድዳችኋል።


የአንተ ሥራ ንጹሕ ደምን ማፍሰስና ሰውን መጨቈን ነው፤ ዐይንህና ልብህም የሚያተኲሩት አጭበርብሮ ትርፍን በማግበስበስ ላይ ብቻ ነው።


ነፍሰ ገዳዮች ንጹሑን ሰው ይጠላሉ፤ ደጋግ ሰዎችንም ለመግደል ይፈልጋሉ።


ቊጣ ጭካኔና ንዴትን ያስከትላል፤ ቅናት ግን ከቊጣ የባሰ ነው።


እጅግ አስፈሪ የሆነ ቊጣቸው፥ እጅግ ጨካኝ የሆነ መዓታቸው፥ የተረገመ ይሁን። በእስራኤል ምድር ሁሉ እበታትናቸዋለሁ፤ በሕዝቡም መካከል እከፋፍላቸዋለሁ።


እርስዋም በእናቷ ተመክራ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን አሁኑኑ ስጠኝ!” አለችው።


ስለዚህ ወደ ወህኒ ቤት ሰው ልኮ የዮሐንስን ራስ በወህኒ ቤት አስቈረጠ።


የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም መጡና በድኑን ወስደው ቀበሩት፤ ሄደውም ይህን ነገር ለኢየሱስ ነገሩት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች