ማቴዎስ 11:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሁሉም ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ ሌላ ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድ ራሱ ፈቅዶ ከሚገልጥላቸው ሌላ አብን የሚያውቅ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። |
ሁሉ ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ወልድንም ማን እንደሆነ ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ አብንም ማን እንደሆነ ከወልድ በቀር ወልድም በፈቃዱ ከሚገልጥለት ሰው በቀር ማንም የሚያውቅ የለም።”