Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 11:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 አዎን አባት ሆይ! ይህ በፊትህ በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አዎን አባት ሆይ፤ ይህ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኗልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 አዎ! አባት ሆይ! ይህን ለማድረግ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 11:26
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሴት አድርጎ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን አባት ሆይ! መልካም ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


“አባት ሆይ! ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ አርቅ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን፤ የአንተ ፈቃድ ይሁን እንጂ፤” እያለ ይጸልይ ነበር።


ኢየሱስም “አባት ሆይ! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፤” አለ። ልብሱንም ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉት።


ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዐይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ! ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ።


“አሁን ነፍሴ ታውካለች፤ ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ! ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።


አባት ሆይ! ስምህን አክብረው።” ስለዚህም “አከበርሁት፤ ደግሞም አከብረዋለሁ፤” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።


እንግዲህ የፈለገውን ይምረዋል የፈለገውንም እልከኛ ያደርገዋል።


እንደ ፈቃዱና እንደ ምክሩ ሁሉን የሚያከናውን እንደ እርሱ ዓላማ የተወሰንን በክርስቶስ በርስትነት ተቀበልን።


በክርስቶስ ለማድረግ የወደደውን የአሳቡን፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናል፤


ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የፈጸመው የዘለዓለም አሳብ ነበረ።


እንደ ሥራችን መጠን ሳይሆን እንደ ራሱ ዕቅድና እንደ ጸጋው መጠን አዳነን፥ በቅዱስም አጠራር ጠራን፤ ይህም ጸጋ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች