በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።
ማርቆስ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ከጀልባ እንደ ወረደ፥ ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ከመቃብር ቦታ ወጣና ወደ እርሱ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከጀልባ እንደ ወረደ፣ ርኩስ መንፈስ ያደረበት ሰው ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ሊገናኘው ወደ እርሱ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ከጀልባው እንደ ወረደ አንድ በርኩስ መንፈስ የተያዘ ሰው ወዲያውኑ ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ተገናኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤ |
በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፥ ምሽቱንም በስውርም ስፍራ የሚያሳልፉ፥ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። ማሰሮዎቻቸው በረከሰ ነገር የተሞሉ ናቸው።
እንደገናም በባሕር ዳርቻ ያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በባሕሩ ላይ በነበረች ጀልባ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ነበሩ።
እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር።