Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ልጁም በመምጣት ላይ ሳለ ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው፤ ልጁንም ለአባቱ መልሶ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ልጁም ወደ ኢየሱስ በቀረበ ጊዜ ጋኔኑ በመሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸው፤ ልጁንም ፈውሶ ለአባቱ ሰጠው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 ሲያ​መ​ጣ​ውም ጋኔኑ ጣለ​ውና አፈ​ራ​ገ​ጠው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠ​ጸው፤ ልጁ​ንም አዳ​ነው፤ ለአ​ባ​ቱም ሰጠው። ሁሉም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅ​ነት የተ​ነሣ አደ​ነቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ሲቀርብም ጋኔኑ ጣለውና አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኵሱን መንፈስ ገሥጾ ብላቴናውን ፈወሰው ለአባቱም መለሰው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:42
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤልያስ ልጁን ከሰገነት ወደ ምድር ቤት አውርዶ ለእናቱ በመስጠት “ተመልከቺ፤ እነሆ ልጅሽ ከሞት ወደ ሕይወት ተመልሶአል!” አላት።


ኤልሳዕም ግያዝን “ሱነማይቱን ጥራ” አለው፤ እርሷም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት።


ሰዎቹም ወደ እርሱ አመጡት፤ ርኩስ መንፈሱም ኢየሱስን ባየው ጊዜ ልጁን ወዲያውኑ አንዘፈዘፈው፤ እርሱም መሬት ላይ ወድቆ በመንፈራገጥም አረፋ ይደፍቅ ጀመር።


የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ፥ ይናገርም ጀመረ፤ ኢየሱስም ጐልማሳውን ለእናቱ ሰጣት።


እነሆም፥ ርኩስ መንፈስ ይይዘዋል፤ ድንገትም ይጮኻል፤ አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ አድቅቆ በጭንቅ ይለቀዋል፤


ኢየሱስም መልሶ፦ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው፤” አለ።


ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ ሳሉ፥ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ፦


ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ከቀዘፉ በኋላም፥ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየተራመደ ወደ ታንኳይቱ ሲቀርብ አይተው ፈሩ።


እጁንም ለእርሷ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።


ስለዚህ ሰማያትና በውስጣቸው የምታድሩ ሆይ! ደስ ይበላችሁ፤ ለምድርና ለባሕር ወዮላቸው፤ ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች