ማርቆስ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል፤” ብለው አሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህ ሰው ለምን እንዲህ ያለ ስድብ በእግዚአብሔር ላይ ይናገራል? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል፤” ብለው አሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ ማን ይችላል? ብለው አሰቡ። |
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱን ትሩፍ ዓመጽ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ርኅራኄ ይወድዳልና ቁጣውን ለዘለዓለም አያቆይም።
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህኑ ልብሱን ቀደደና እንዲህ አለ “ተሳድቦአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ምስክሮችን መያዝ ለምን ያስፈልገናል? እነሆ አሁን ስድቡን ሰምታችኋል፤
ጻፎችና ፈሪሳውያንም፦ “ስድብን የሚሰነዝር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ ማን ኃጢአትን ሊያስተሰርይ ይችላል?” እያሉ ያስቡ ነበር።
አይሁድም “ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ እንጂ፤ ይልቁንም አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ እራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው” ብለው መለሱለት።