Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 10:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አይሁድም “ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ እንጂ፤ ይልቁንም አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ እራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አይሁድም፣ “የምንወግርህ፣ ተራ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ በማድረግ፣ የስድብ ቃል ስለ ተናገርህ ነው እንጂ ከእነዚህ ስለ የትኛውም አይደለም” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እነርሱም “እኛ የምንወግርህ በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ስለ መናገርህ ነው እንጂ ስለ መልካም ሥራህ አይደለም፤ ይኸውም አንተ ሰው ሆነህ ሳለ፥ ራስህን አምላክ ስላደረግህ ነው” ሲሉ መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ፥ ሰው ስት​ሆን ራስ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ር​ጋ​ለ​ህና፤ ስለ መሳ​ደ​ብህ ነው እንጂ ስለ መል​ካም ሥራ​ህስ አን​ወ​ግ​ር​ህም” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አይሁድም፦ “ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ” ብለው መለሱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 10:33
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ደግሞ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ “እግዚአብሔር አባቴ ነው፤” ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።


የጌታንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የአገሩ ተወላጅ ቢሆን፥ የጌታን ስም በሰደበ ጊዜ ይገደል።


እኔና አብ አንድ ነን።”


እርሱ የእግዚአብሔር ባሕርይ ኖሮት ሳለ እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር እኩልነትን እንደመንጠቅ አድርጎ አልቈጠረውም፤


ሁሉም ሰው ለበላይ ባለ ሥልጣናት ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።


እኔ ግን፦ አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ አልሁ፥


የአዴርም ልጅ፦ “ለሚከተለኝ ሕዝብ የሰማርያ ትቢያ ጭብጥ ጭብጥ ይበቃው እንደሆነ፥ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ ይህንም ይጨምሩብኝ” ብሎ ላከበት።


“ተሳዳቢውን ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው።


አይሁድም እርሱን ከብበው “እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሬ ታቆየናለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ በግልጥ ንገረን፤” አሉት።


ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።


አይሁድም መልሰው “እኛ ሕግ አለን፤ በሕጋችን መሠረት ሊሞት ይገባዋል፤ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ አድርጎአልና” አሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች