እነርሱም፦ “ለራስህ ቁም፥ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ” ይላሉ፤ እነዚህ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት፥ በአፍንጫዬ ስር የምታልፍ ጢስ ናቸው።
ማርቆስ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድነው?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈሪሳውያን ጸሐፍት ከኀጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋራ ሲበላ ባዩት ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ይበላል?” ሲሉ ጠየቋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ የሕግ መምህራን ኢየሱስ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው “ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው ስለምንድን ነው?” በማለት ደቀ መዛሙርቱን ጠየቁአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ “ከቀራ ጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው?” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጻፎችና ፈሪሳውያንም ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ሲበላ አይተው ለደቀ መዛሙርቱ፦ ከቀራ ጮችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላና የሚጠጣ ስለ ምንድር ነው? አሉ። |
እነርሱም፦ “ለራስህ ቁም፥ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ” ይላሉ፤ እነዚህ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት፥ በአፍንጫዬ ስር የምታልፍ ጢስ ናቸው።
ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እንደ ሌሎች ሰዎች ሁሉ፥ ቀማኛና ዐመፀኛ አመንዝራም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤
ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።