ማርቆስ 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም፥ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን፥ “ስቀለው” እያሉ የባሰ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን የፈጸመው ወንጀል አለ” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው!” እያሉ የባሰ ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም “ለምን? ያደረገው በደል ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም “ስቀለው!” እያሉ አብዝተው ጮኹ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አላቸው። እነርሱ ግን “ስቀለው!” እያሉ ጩኸት አበዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱ ግን፦ ስቀለው እያሉ ጩኸት አበዙ። |
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ፥ ሚስቱ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ተሠቃይቻለሁና በዚያ ጻድቅ ላይ ምንም እንዳታደርግ” ስትል ላከችበት።
የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አሉ።
እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።
የካህናት አለቆችና ሎሌዎችም ባዩት ጊዜ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት” አላቸው።