ሉቃስ 5:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስላጠመዱት ዓሣ ተደንቀው ነበርና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያለው እርሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት በያዙት ዓሣ ብዛት ስለ ተደነቁ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያለበት ምክንያት እርሱና አብረውት የነበሩት ጓደኞቹ ሁሉ ከያዙት ዓሣ ብዛት የተነሣ እጅግ ተገርመው ስለ ነበር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ስለ ተያዘው ዓሣ ተደንቀው ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስላጠመዱት ዓሣ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩ ሁሉ ተደንቀዋልና፥ |
ሁሉም ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፦ “ይህ ቃል ምንድነው? በሥልጣንና በኃይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፥ እነርሱም ይወጣሉ፤” እያሉ ይነጋገረሩ ነበር።
እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ወዳጆች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።