ሉቃስ 4:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገብዋም ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ወዲያውም ተነሥታ አገለገለቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወደ ተኛችበት ጠጋ ብሎ በማጐንበስ ትኵሳቱን ገሠጸው፤ ትኵሳቱም ለቀቃትና ወዲያው ተነሥታ አስተናገደቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ወደ እርስዋ ቀርቦ አጠገብዋ ቆመና ትኲሳቱ እንዲለቃት አዘዘ፤ ትኲሳቱም ለቀቃት፤ ወዲያውኑም ተነሥታ ታስተናግዳቸው ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገብዋም ቁሞ ንዳድዋን ገሠጸውና ተዋት፤ ወዲያውም ተነሥታ አገለገለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው። |
አጋንንትም ደግሞ፦ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው እየጮኹ ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ እርሱ ግን ገሠጻቸው፤ እንዲናገሩም አልፈቀደላቸውም፥ ምክንያቱም ክርስቶስ እንደሆነ አውቀውት ነበርና።
ቀርበውም፦ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! እየጠፋን ነው፤” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚናውጠውን የውኃ ሞገድ ገሠጻቸው፤ እነርሱም አቆሙ፤ ጸጥታም ሆነ።