Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 4:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 እርሱም ወደ ተኛችበት ጠጋ ብሎ በማጐንበስ ትኵሳቱን ገሠጸው፤ ትኵሳቱም ለቀቃትና ወዲያው ተነሥታ አስተናገደቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 በአጠገብዋም ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ወዲያውም ተነሥታ አገለገለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ኢየሱስም ወደ እርስዋ ቀርቦ አጠገብዋ ቆመና ትኲሳቱ እንዲለቃት አዘዘ፤ ትኲሳቱም ለቀቃት፤ ወዲያውኑም ተነሥታ ታስተናግዳቸው ጀመር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 በአጠገብዋም ቆሞ ንዳዱን ገሠጸውና ለቀቃት፤ ያንጊዜውንም ተነሥታ አገለገለቻቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 4:39
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ዝም በልና ከእ​ርሱ ውጣ” ብሎ ገሠ​ጸው፤ ጋኔ​ኑም በም​ኵ​ራቡ መካ​ከል ጣለ​ውና ከእ​ርሱ ወጣ፤ ነገር ግን ምንም አል​ጐ​ዳ​ውም።


ቀር​በ​ውም፥ “መም​ህር ሆይ፥ መም​ህር ሆይ፥ ልን​ጠፋ ነው” ብለው ቀሰ​ቀ​ሱት፤ ተነ​ሥ​ቶም ነፋ​ሱ​ንና የው​ኃ​ዉን ማዕ​በል ገሠ​ጻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ ታላቅ ፀጥ​ታም ሆነ።


ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች