ኢየሱስም መልሶ፦ “ ‘ጌታን አምላክህን አትፈታተነው፤’ ተብሏል፤” አለው።
ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሏል” ብሎ መለሰለት።
ኢየሱስም፦ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው፥’ ተብሎ ተጽፎአል፤” ሲል መለሰለት።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ፈጣሪህ እግዚአብሔርን አትፈታተነው” ተብሎአል አለው።
ኢየሱስም መልሶ፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎአል አለው።
በምድረ በዳም በምኞትን ተቃጠሉ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።
የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ምንም እንኳን ሥራዬን ቢያዩም ፈተኑኝ።
አሁንም ትዕቢተኞችን የተባረኩ ብለን እንጠራቸዋለን፤ ክፉንም የሚሠሩ ታንጸዋል፥ እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም።
ኢየሱስም “‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል” አለው።
ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ለጊዜው ከእርሱ ተለየ።
ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባቦች እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን።
“ ‘በማሳህ’ እንደ ፈተናችሁት ጌታ አምላካችሁን አትፈታተኑት።