እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ሉቃስ 24:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየባረካቸውም ከእነርሱ ተለየ፤ ወደ ሰማይም ዐረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እየባረካቸውም ሳለ፣ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲባርካቸውም ሳለ ከእነርሱ ተለይቶ ወደ ሰማይ ዐረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እየባረካቸውም ራቃቸው፤ ወደ ሰማይም ዐረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። |
እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ኢየሱስም “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ፤’ ብለሽ ንገሪአቸው፤” አላት።