ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።
ሉቃስ 19:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችም እርሱ በሚሄድበት መንገድ ላይ ልብሶቻቸውን ያነጥፉ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ሲሄድ ሳለ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገዱ ላይ ያነጥፉለት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሄዱም በመንገድ ልብሳቸውን አነጠፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር። |
ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።
ወደ ደብረዘይት ቁልቁለትም ወዲያው በቀረበ ጊዜ፥ ደቀመዛሙርቱ በሙሉ ስላዩአቸው ተአምራት ደስ እያላቸው በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመሩ፤