ሉቃስ 18:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ እያለፈ ነው፤” ብለው አወሩለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም “እነሆ! የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ያልፋል ብለው አወሩለት። |
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁት፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤
እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።