Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 19:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ጲላጦስም ጽሑፍ ጽፎ በመስቀሉ ላይ አንጠለጠለው፤ ጽሑፉም፣ “የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጲላጦስ “የናዝሬቱ ኢየሱስ፥ የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ጽሑፍ ጽፎ በመስቀሉ ራስጌ ላይ አኖረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ጲላ​ጦ​ስም ጽሕ​ፈት ጽፎ በመ​ስ​ቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ” የሚል ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም፦ “የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ” የሚል ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 19:19
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተከሰሰበትንም ምክንያት “ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው” የሚል ጽሑፍ ከራሱ በላይ አኖሩ።


“ይህ የአይሁድ ንጉሥ ነው፤” የሚል በግሪክ፥ በሮማይስጥና በዕብራይስጥ ፊደል የተጻፈ ጽሕፈት ደግሞ በእርሱ ላይ ነበረ።


የክሱ ጽሑፍም፥ “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ነበር።


የፋሲካም በዓል የሚዘጋጅበት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ አይሁድንም “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው።


ጴጥሮስ ግን “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ፤” አለው።


ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን “እርሱ ‘የአይሁድ ንጉሥ ነኝ’ አለ ብለህ ጻፍ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ፤” አሉት።


ከዚህ በኋላ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፤ ነገር ግን አይሁድ “ይህን ሰው ከፈታኸው የቄሣር ወዳጅ አይደለህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚያደርግ ሁሉ የቄሣር ተቃዋሚ ነው” እያሉ ጮኹ።


እየቀረቡም “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር።


ጲላጦስም እንደገና ወደ ገዢው ግቢ ገባና ኢየሱስን ጠርቶ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።


ናትናኤልም መልሶ “መምህር ሆይ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ” አለው።


“እኔም ራሴ የናዝሬቱን የኢየሱስን ስም የሚቃወም እጅግ ነገር አደርግ ዘንድ እንዲገባኝ ይመስለኝ ነበር።


በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው እንዲፈጸም፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


እነርሱም “የናዝሬቱ ኢየሱስ እያለፈ ነው፤” ብለው አወሩለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች