ሉቃስ 14:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ መደምደም አቃተው፤’ ብለው ሊቀልዱበት ይጀምራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ይላሉ፤ ‘ይህ ሰው ማነጽ ጀምሮ ነበር፤ መደምደም ግን አቃተው።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እነሆ፥ ይህ ሰው ቤት መሥራት ጀምሮ መጨረስ አልቻለም’ እያሉ ያፌዙበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘ይህ ሰው ሊሠራ ጀመረ፤ ግን መጨረስ ተሳነው’ እያሉ ሊዘብቱበት ይጀምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ። |
ወይንም በጦርነት ሌላውን ሊጋጠም የሚሄድ ንጉሥ፥ ሃያ ሺህ ሰው አስከትቶ የሚመጣበትን በዐሥር ሺህ ሰው ሊገጥም ይችል እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ማን ነው?