ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?
ሉቃስ 11:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ ዘንድ አንዳንዶች ግን፦ “በብዔልዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ ግን፣ “በአጋንንት አለቃ፣ በብዔልዜቡል፣ አጋንንትን ያወጣል” አሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንዶች ግን “አጋንንትን የሚያስወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል ነው፤” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከመካከላቸው፥ “በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣቸዋል” ያሉ ነበሩ፤ እርሱም መልሶ፥ “ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዱ፦ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ። |
ደቀመዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባርያም እንደ ጌታው ከሆነ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔልዜቡል ካሉት፥ ቤተሰቦቹንማ እንዴት ከዚህ የበለጠ አይሉአቸው?
ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።