የአሞንም ልጆች ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ገቡ። ኢዮአብም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
ዘሌዋውያን 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በጦርነት ያልቃሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፤ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በፊታችሁም በሰይፍ ይወድቃሉ። |
የአሞንም ልጆች ሶርያውያን እንደ ሸሹ ባዩ ጊዜ እነርሱ ደግሞ ከወንድሙ ከአቢሳ ፊት ሸሹ፥ ወደ ከተማይቱም ገቡ። ኢዮአብም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
“ጌታ በአንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶችህን በፊትህ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ አቅጣጫ ይመጡብሃል፤ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫም ከአንተ ይሸሻሉ።
ባራቅ ግን የሲሣራን ሠረገሎችና ሠራዊቱን እስከ ሐሮሼት ሐጎይም ድረስ አሳደዳቸው፤ የሲሣራ ሠራዊት በሙሉ በሰይፍ ወደቀ፤ በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።
ዮናታን በእጁና በእግሩ ወደ አፋፉ፥ ጋሻ ጃግሬውን በማስከተል ወጣ። በዮናታንም እጅ ወደቁ፤ ጋሻ ጃግሬውም ከበስተኋላው እየተከተለ ገደላቸው።