ዘሌዋውያን 25:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ እንደ መከሩ ቍጥር ይሸጥልሃልና ዓመታቱ ብዙ በሆኑ ቍጥር ዋጋውን ከፍ ታደርጋለህ፥ ዓመታቱ ግን ባነሱ ቍጥር ዋጋውን ታሳንሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዓመቱ ቍጥር ከበዛ ዋጋውን ጨምር፤ የዓመቱ ቍጥር ካነሰም፣ ዋጋውን ቀንስ፤ ምክንያቱም የሚሸጥልህ የዓመቱን የምርት መጠን ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓመታቱ ብዙ ቢሆኑ፥ ዋጋው ከፍ ይላል፤ ዓመታቱ ጥቂቶች ከሆኑ ዋጋው ዝቅ ይላል፤ የሚሸጥበት ዋጋ የሚተመነው ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል መጠን ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ዓመታቱ ብዛት ዋጋውን ያበዛል፤ እንደ ዓመታቱም ማነስ ዋጋውን ያሳንሳል፤ እንደ መከሩ ቍጥር ይሸጥልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ዓመታቱ ማነስ ዋጋውን ታሳንሳለህ፤ እንደ መከሩ ቍጥር ይሸጥልሃል። |
ነገር ግን እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ቊጥር ገንዘቡን ያስላልህስ፤ ከዚያም ከግምትህ ላይ ይቀነሳል።