Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 27:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነገር ግን እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ቊጥር ገንዘቡን ያስላልህስ፤ ከዚያም ከግምትህ ላይ ይቀነሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዕርሻውን የሚቀድሰው ከኢዮቤልዩ በኋላ ከሆነ ግን፣ ካህኑ ዋጋውን የሚተምነው እስከሚመጣው የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ባሉት ዓመታት ቍጥር ልክ ነው፤ የተተመነውም ዋጋ ይቀነሳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 መሬቱን የሰጠው የኢዮቤልዩ ዓመት ካለፈ ዘግይቶ ከሆነ ግን ካህኑ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ቀሪ ጊዜ በመገመት ዋጋው እንዲቀነስ ያድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት በኋላ ቢሳል፥ ካህኑ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመ​ታት ገን​ዘ​ቡን ይቈ​ጥ​ር​ለ​ታል፤ ከግ​ም​ቱም ይጐ​ድ​ላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት በኋላ ቢቀድስ፥ ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ እንደ ቀሩት ዓመታት ገንዘቡን ይቈጥርለታል፤ ከግምቱም ይጐድላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 27:18
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም እስከ ሸጠበት ጊዜ ያሉትን ዓመታት ያሰላል፥ ከዚያም የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልሳል፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።


“ለጌታም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ሰው ቤቱን ቢቀድስ፥ ካህኑ መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይጸናል።


እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምትህ መጠን ይጸናል።


እርሻውንም የቀደሰ ሰው ሊቤዠው ቢወድድ፥ በገመትከው የገንዘብ መጠን ላይ አምስት እጅ ይጨምራል፤ ከዚያም ለእርሱ ይጸናለታል።


ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ያሰላለታል፤ በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለጌታ ይሰጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች