ዘሌዋውያን 20:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቅደሴን ለማርከስ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ለማንቋሸሽ ልጁን ለሞሌክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁን ለሞሎክ በመስጠት መቅደሴን አርክሷልና፣ ቅዱሱን ስሜንም አቃልሏልና፣ በዚያ ሰው ላይ ጠላት እሆንበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሌክ አሳልፎ በመስጠት የተቀደሰውን ድንኳኔን ቢያረክስና ቅዱስ ስሜንም ቢያሰድብ፥ ያ ሰው በእኔ ፊት የተጠላ ይሆናል፤ ከሕዝቡም ለይቼ አጠፋዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የቅዱሳኔንም ስም ያጐስቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ያጐሰቁል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።
“እንዲሁም በመካከላቸው የምትገኘውን የመገናኛዬን ድንኳን በማርከስ በርኩስነታቸው እንዳይሞቱ፥ እናንተ የእስራኤልን ልጆች ከርኩስነታቸው ለዩአቸው።”
“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሆናሉ፥ የአምላካቸውንም ስም አያረክሱም፤ እነርሱም የአምላካቸው እንጀራ የሆነውን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያቀርባሉና የተቀደሱ ይሆናሉ።
ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”
የሞተውን ሰው በድን የነካ ማናቸውም ሰው ሁለመናውን ባያነጻ የጌታን ማደሪያ ያረክሳል፤ ያ ሰው ከእስራኤል ዘንድ ተለይቶ ይጠፋል፤ በእርሱም ላይ ከርኩሰት የሚያነጻ ውኃ አልተረጨምና ርኩስ ይሆናል፤ ርኩሰቱ ገና በእርሱ ላይ ነው።
“ሰውም ርኩስ ቢሆን ሁለመናውንም ባያነጻ፥ ያ ሰው የጌታን መቅደስ አርክሶአልና ከጉባኤው መካከል ተለይቶ ይጠፋል፤ ከርኩሰት የሚያነጻውን ውኃ አልተረጨም፤ ርኩስ ነው።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።